አዝ፦ ከእንቅልፌ ነቅቸ ዓይኔን እንደገለጥኩ ዓለም እንዴት ብዬ ራሴን ጠየቅሁ ዘገባው ምን ይሆን ደግሞ የሚጠብቀኝ እስቲ ዜና ላዳምጥ ትንሽ ሬዲዮ አለኝ ርዕስ ዜናዎች ብሎ እንደጀመረ ፍርሃት ፍርሃት አለኝ ልቤ ተሸበረ ያው እንደጠበቅኩት መልካም ወሬ የለም የለቅሶ የሃዘን የስብራት የደም ጊዜው ጊዜው ጊዜው (2x) የጊዜው ምልክት ወቅቱና ዘመኑ የሬዲዮ ዜና የማታው የቀኑ ያየነው በቲቪ የጋዜጣው ወሬ መልካም ቀን ተወልዷል ከትናንቱ ዛሬ ዋ ጊዜው ኦሆሆ ጊዜው ስንቱን አሳየን ጊዜው መስከረም አስራ አንድ ገና በማለዳ አይሮፕላን ጥሶ የህንጻ ግድግዳ በፍራቻ ሆነው አእላፍ እያዩ መንትዮቹ ህንጻዎች ፈራረሱ ጋዩ ልጆቹዋንእባሕር ያሰጠመች እናት ጭካኔቅ ግፍዋ ሲተረክ በጠዋት ትምህርት ቤት ሰለተጋደሉት ዜናው ሲያነበንብ በአንክሮት ሰማሁት አዝ፦ ከእንቅልፌ ነቅቸ ዓይኔን እንደገለጥኩ ዓለም እንዴት ብዬ ራሴን ጠየቅሁ ዘገባው ምን ይሆን ደግሞ የሚጠብቀኝ እስቲ ዜና ላዳምጥ ትንሽ ሬዲዮ አለኝ የሩዋንዳው እልቂት በሺ ዘጠና አራት በሰነበት ቂም በዘር ቁርሾ ማክንያት የዳርፉር እናቶች ዛሬም ደጅ ናቸው የበረሃ አቡዋራ እየገረፋቸው ፍልስጤም ከእስሬኤል ዛሬም እልታረቀ በመካከለኛው ምስራቅ ዛሬም ስንቱ አለቀ የሰው ፈንጂ ሆኖዋል ምድርን ያስጨንቃት ራሱ እንደጡዋፍ ነዶ አጥፍቶ ለማጥፋት አዝ፦ ከእንቅልፌ ነቅቸ ዓይኔን እንደገለጥኩ ዓለም እንዴት ብዬ ራሴን ጠየቅሁ ዘገባው ምን ይሆን ደግሞ የሚጠብቀኝ እስቲ ዜና ላዳምጥ ትንሽ ሬዲዮ አለኝ የጦርነት የሁካታ ወሬ በዝቶ ዝናብ ጠፍቶ ምድር ደርቃ ችጋር ገብቶ ልጅ ከወለደች ባል ከሚስቱ ተከዳድቶ ገንዘብ ነግሶ መተማመን ከምድር ጠፍቶ ይህ ጊዜያዊ መኖርያችን ተውሳክ ቦታ ማብቂያው ቀርቧል ሊገለጥ ነው የድል ጌታ የምናየው የምንሰማው ይቀስቅሰን እንዘጋጅ ለምጽአቱ ለታላቅ ቀን