የነጻነት መዘዝ የአምልኮ ነጻነት በበጐቹ መግቢያ ትኩሎች ዘው አሉበት ሥርዓት የሌለበት ገደብ የሌለበት የኢየሱስ ሥም ለንግድ ጨረታ የወጣበት አወይ ነጻነት አወይ ነጻነት አወይ ነጻነት ለአምልኮ ነጻነት ሱባኤ ተገብቶ መሰደድም ቀረ ከላይ ትዕዛዝ ወጥቶ መግቢያ በሩ ሰፋ ሰው ተግተለተለ እንክርዳዱ ስንዴ ተኩላው በግ መሰለ የድል አጥቢያ አርበኛ ዘለቀ ሆ ብሎ ውጪያዊ ምስሉን ወጉን አስተካክሎ በየጓዳው ፈላ ቤተክርስቲያን ሰሪ ራሱ ፈላጭ ቆራጭ ባለሚኒስትሪ ዶክትሪኑ በዛ መድረክ ጠበበ ጥራት ሳይሆን ብዛት ስንቱን ሰበሰበ ግርግር እንዳይሉት ወይ ዘመነ ጥፉ የአምልኮ ነጻነት ብለውት አረፉ ኦሆ ኦሆ ነጻነት ነጻነት እያሉ ሲያሞግሱሽ ዋሉ ጉድሽ ግን ብዛቱ ላወቀው ለስንቱ የነጻነት መዘዝ የአምልኮ ነጻነት በበጐቹ መግቢያ ትኩሎች ዘው አሉበት ሥርዓት የሌለበት ገደብ የሌለበት የኢየሱስ ሥም ለንግድ ጨረታ የወጣበት አወይ ነጻነት አወይ ነጻነት አወይ ነጻነት መጽሃፍ ቅዱስ ኮሌጅ አጠናቅቄያለሁ ምስክር ወረቀት ቆቤንም ጭኛለሁ አንግዲህ የቀረኝ ሀያ ሰው ሰብስቤ ኪሳቸው ኪሴ ነው ለወጭ ለቀለቤ እያሉ የሚያልሙ ወንጌል ተጡዋሪዎች ዙሪያችን ፈልተዋል ሥራ ጠላቱዎች (2x) ቀላዋጮች ብዙ ተንባዮች ለእንጐቻ መረቅ ላጠጣቸው ላበላቸው ብቻ እንደ መተተኛ እዚህ እዛ እያሉ ቅልጥም ላገኙበት ይተነብያሉ የነጻነት ውልዶች ስንቱን ያሞኛሉ በግርግር መጥተው የተቀላቀሉ የተቀላቀሉ ኦሆ ኦሆ ነጻነት ነጻነት እያሉ ሲያሞግሱሽ ዋሉ ጉድሽ ግን ብዛቱ ላወቀው ለስንቱ የነጻነት መዘዝ የአምልኮ ነጻነት በበጐቹ መግቢያ ትኩሎች ዘው አሉበት ሥርዓት የሌለበት ገደብ የሌለበት የኢየሱስ ሥም ለንግድ ጨረታ የወጣበት አወይ ነጻነት አወይ ነጻነት አወይ ነጻነት ራሱን የሚያዳንቅ አገልጋይሞልቶናል ሥሙን ሲያስተዋውቅ ፎቶውን አይተናል ስብከቴ ነክቶአቸው እልፍ ሰዎች ዳኑ አጋንንቶች ወጡ ብሎ ማጋነኑ ራሱ እንዳደረገው በኃይል በጥበቡ እውቁልኝ ብሎ ሥሙን ማነብነቡ (2x) ባለድርጂቱስ በጐ አድራጊ መሳይ በሙት ልጆች ነጋጅ ጫና ጫንቃቸው ላይ በድሀ ሥም ዞሮ ባከማቸው ሁሉ ፎቁን ገንብቶበት የሚታይ ለሁሉ ምናልባት ሲተርፈው ከርሱን ካጠገበ ትርፍራፊው ሲቀር ድሆቹን አሰበ ኦሆ ኦሆ ነጻነት ነጻነት እያሉ ሲያሞግሱሽ ዋሉ ጉድሽ ግን ብዛቱ ላወቀው ለስንቱ ላወቀው ለስንቱ (2x) ጉድሽ ግን ብዛቱ ላወቀው ለስንቱ ላወቀው ለስንቱ (2x)