የአድናቆት ቀን ለእግዚአብሔር ለወደደን የሚገባው እርሱ ነው እውነቱን እንወቅ ጠንቅቀን ጀብዱው ገድሉ የሚወራለት ጭፍራ አለቃው የሚስግዱለት እግዚአብሔር ምሥጉን ሥም ያለው አድናቆቱም ምሥጋናውም መገረሙም ለእርሱ ሥም ነው ማነው ፍጥረትን የሰራ ሰማይ ምድርን የቀየሰው ማነው በአፍንጫው እፍ ያለ የሕይወትን እስትንፋስ ለሰው ማነው ነፋስን አንፋሹ የእሳት የውሃው አለቃ ማነው አዛዥ የጸሀይዋ ማነው አዛዥ የጨረቃ ማነው የምድርን ዳርቻ በእጆቹ መዳፍ ያኖረ ማነ ፈርዖንን በዝቅጠት በውኃ በታች ያስቀረ ማነው ከፍታን የሚያዘው ዝቅታም የሚያረግድለት ማነው ብድራትን መላሽ ከቅርብ ወይም ከርቀት እግዚአብሔር (4x) ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር አንተ ብቻ አንተ ክብር (3x) አለቆች የምድር ፈርጆች ጐልማሶች ቆነጃጅቶች እሳትና በረዶ አመዳይ ጨምሮም ውርጮች ተራሮችና ኮረብቶች ፍሬ የሚያፈሩ ዝግቦች በቃሉ ሲንቀጠቀጡ እዩት ሲያደንቁት ፍጥረቶች ማነው የዋሁን ታዳጊ መመኪያ ለቅዱሳኑ ማነው ቅን ፈራጅ መጠጊያ ለሥሙ ታምነው ለጸኑ ማነውጉሙን የሚበትን የአንበሳን መንጋጋ ያደቀቀ ማነው ወጥመድን ሰባሪ ህዝቡን ከግዞት የጠበቀ እግዚአብሔር (4x) ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር አንተ ብቻ አንተ ክብር (3x)