Song Lyrics

ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም

Dereje Kebede
Mengiste Semay
አዝ፦ ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም የጌታ ፀጋ አላነሰንም ዲያቢሎስ ቢራቀቅ ቢመጥቅ በእጥፍ አይተኛም እኛን ሚጠብቅ (2x) እርግጥ ነው ጠላታችን እጅግ ተራቋል መተላለፊያውን ሰውሮ አስቀምጧል ምድርን በእጁ አድርጐ ይጫወትባታል ለእኛ ግን እግዚአብሔር እንዳለን ተረድቷል አዝ፦ ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም የጌታ ፀጋ አላነሰንም ዲያቢሎስ ቢራቀቅ ቢመጥቅ በእጥፍ አይተኛም እኛን ሚጠብቅ (2x) ሃያ እጥፍ ቢያነድም እሳቱን ሊያስበላን የሚያጠውፋው ውኃ ኢየሱስ አለልን ባህሩን ቢያሰፋ ሊያሰምጠን ወደስር እርግብ ሆኖ ማዶ አለን የሚያሻግር አዝ፦ ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም የጌታ ፀጋ አላነሰንም ዲያቢሎስ ቢራቀቅ ቢመጥቅ በእጥፍ አይተኛም እኛን ሚጠብቅ (2x) ምድርን ለቆ ሰይጣን በአየር እየሮጠ ሊያዳክም አማኝን በሩን ቀጠቀጠ የክርስቲያን መዝጊያው አይበገር ኖሮ መና ቀረ ጠላት ያለ ኃይሉን ጥሎ አዝ፦ ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም የጌታ ፀጋ አላነሰንም ዲያቢሎስ ቢራቀቅ ቢመጥቅ በእጥፍ አይተኛም እኛን ሚጠብቅ (2x) ወጥመዱ በርትቶ ሊያጠምደን ቢጣጣር ሕያው አምላካችን ይዋጋል ከእኛ ጋር የጽዮን አርበኛ ቆራጥ እየታጠቀ አንዴ ማን ተረታ አንዴ ማን ወደቀ አዝ፦ ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም የጌታ ፀጋ አላነሰንም ዲያቢሎስ ቢራቀቅ ቢመጥቅ በእጥፍ አይተኛም እኛን ሚጠብቅ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection