ዝ፦ እንደ ሌባ እንደ ወንጀለኛ ንጹህ አምላክ ሆነልን ስለእኛ በጨለማ በድቅድቁ ሳለን በእግዚአብሔር ኢየሱስን አገኘን (2x) እጅግ ከብዶት ነበረ መስቀሉ አሸክመው ሲያስጨንቁት ዋሉ ለዓለም ኃጢአት ኢየሱስ ተመታ በመስቀል ሞት በእርባን እንዲፈታ (2x) የደሙ ላብ አለዋጋ አይደለም የጐኑ ውኃ ለከንቱ አልፈሰሰም ንጹህ ደሙ ለእንስሳት አይደለም ክቡር ማንጻት አለው ለእኔም ለአንተም (2x) አዝ፦ እንደ ሌባ እንደ ወንጀለኛ ንጹህ አምላክ ሆነልን ስለእኛ በጨለማ በድቅድቁ ሳለን በእግዚአብሔር ኢየሱስን አገኘን (2x)