አዝ፦ ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ እራሱን አዋርዶ (2x) ደቀ መዛሙርቱ አግራቸው ቆሸሸ አደፈ ጐደፈ ፍፁም ተበላሸ ሁሉን የፈጠረ ሰውን የወደደ ጭቃውን ሊያስወግድ ወደታች ወረደ አዝ፦ ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ እራሱን አዋርዶ (2x) እርሱ ያላጠበው ከእርሱ ጋር አይኖርም አይቆርስም ከአምላክ ጋራ አንድነት የለውም ጴጥሮስ ይህን አይቶ ሰውነቴን ደግሞ እጠበኝ ጌታ ሆይ አለውም ተማጽኖ አዝ፦ ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ እራሱን አዋርዶ (2x) በሚደነቅ ብርሃን የሚኖር ፈጣሪ አልፋና ኦሜጋ የፍጥረታት ሰሪ ማበሻ ጨርቅ ወስዶ እግር ሊያጥብ ወረደ ዝቅ አደረገ እራሱን ለሰው አዋረደ አዝ፦ ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ እራሱን አዋርዶ (2x) የሁሉ ማሰሪያ አላማ ያለው ነው ጌታ ይህን አድርጓል እኔስ እንደምነው የወንድሜን እግር እስካጥብ ዝልቅ ካልኩ እውነትም ኢየሱስን በእርግጥ ተከተልኩ አዝ፦ ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ እራሱን አዋርዶ (2x) ባሪያ ከሚያኖረው አይበልጥም አላቸው መልዕክተኛም አይበጅ ይልቁን ከላከው እንግዲህ ጌታችሁ እኔ ይህን ስፈጽም አድርጉት ለሁሉም ዛሬ ሁኑ እናንተም አዝ፦ ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ እራሱን አዋርዶ (2x)