ቅብዝብዝነትን አጣሁት ከላዬ መንፈስ ቅዱስ ገዛው ዘልቆ ልቦናዬን ኃይልን ከአርያም መልበሴን የማውቀው የማልፍበት ሰላም ስላልተለየኝ ነው አዝ፦ ሰላም አለኝ እንደወንዝ እንደወንዝ የሚፈስ አዕምሮዬን የሚያረሰርስ ደስታ አለኝ ከውስጤ ከውስጤ ማይጠፋ ኢየሱስ ክብሩ ይስፋ ኡኡኡኡኡ (2x) ማነው የሚነጥቀኝ ይህንን ጸጥታ የማይለየኝ ከውስጤ ለአንድ አፍታ ከሰማይ ተገኝቶ ሰማያዊ የሆነ ምድራዊማ ይሄኔ ትቶኝ በተነነ አዝ፦ ሰላም አለኝ እንደወንዝ እንደወንዝ የሚፈስ አዕምሮዬን የሚያረሰርስ ደስታ አለኝ ከውስጤ ከውስጤ ማይጠፋ ኢየሱስ ክብሩ ይስፋ ኡኡኡኡኡ (2x) እግዚአብሔር ይመስገን እንቅልፌን እተኛለሁ አደራዬን ለእርሱ ላምለኬ እጥላለሁ የብረት መዝጊያዬ ኢየሱስ ሆኖልኛል በእርሱ ተሸሽጌ ምንስ ይደፍረኛል አዝ፦ ሰላም አለኝ እንደወንዝ እንደወንዝ የሚፈስ አዕምሮዬን የሚያረሰርስ ደስታ አለኝ ከውስጤ ከውስጤ ማይጠፋ ኢየሱስ ክብሩ ይስፋ ኡኡኡኡኡ (2x) ጌታ መሠረቴ የማይነቃነቅ ድጋፍ መፅናኛዬ የሚያነሳኝ ስወድቅ መናወጥ ከልቤ ተፍቶል ላይመለስ የሰላሜ ጌታ ይመስገን ኢየሱስ አዝ፦ ሰላም አለኝ እንደወንዝ እንደወንዝ የሚፈስ አዕምሮዬን የሚያረሰርስ ደስታ አለኝ ከውስጤ ከውስጤ ማይጠፋ ኢየሱስ ክብሩ ይስፋ ኡኡኡኡኡ(2x)