Song Lyrics

ማረን አቤቱ

Dereje Kebede
Mengiste Semay
አዝ፦ ማረኝ ጌታ ሆይ ማረኝ አቤቱ ከመዓቱ (2x) እንደሎጥ አድነኝ እንደኖህ አድነኝ አንደበቴ ረክሶ ሰላሜን ነጠቀኝ ስንዴነቴን እንጃ እንክርዳድ ብቻ ነኝ (2x) አዝ፦ ማረኝ ጌታ ሆይ ማረኝ አቤቱ ከመዓቱ (2x) ጌታ ሆይ አየሁኝ ጊዜ ያሳይ የለ ያ ሁሉ ግለቴ??? ተሟጦ የታለ ቀኑን ሙሉ ልቤ አንተን እንዳላለ (2x) አዝ፦ ማረኝ ጌታ ሆይ ማረኝ አቤቱ ከመዓቱ (2x) ቃልህን ህግህን እግሬ ስር ጥያለሁ እንደ ሥጋ ፈቃዴም እመላለሳለሁ ማረኝ እንደገና እማጸንሃለሁ (2x) አዝ፦ ማረኝ ጌታ ሆይ ማረኝ አቤቱ ከመዓቱ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection