Song Lyrics

ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል

Dereje Kebede
Mengiste Semay
አዝ፦ ጌታ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል በስምህ ትዕዛዝ ስር ያድራል በልቡ አንተን ፈላጊ ስምህን ጠሪ ይባረካል በኑሮ የሚያስቀድምህ የደስታን ካባን ይደርባል ከእርኩሰት ታርቀዋለህ በልቡ ዙፋን ላይ ነግሰህ ሰላምን በውስጡ አኑሮ ይጓዛል ደስታን ጨምሮ አዝ፦ ጌታ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል በስምህ ትዕዛዝ ስር ያድራል ከኋለኛው ሃዘን ይልቅ የአሁኑን ጉስቁልና መርጦ ጊዜያዊውን ተድላ ንቆ ነፍሱን ከሥጋው ያየ አብልጦ ብልህ ነው ጠቢብ አዋቂ የሰማይ ሃገር ዘላቂ ዘለዓለም እረፍትን አይቷል ለተስፋው ምድር ተመርጧል አዝ፦ ጌታ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል በስምህ ትዕዛዝ ስር ያድራል በለመለመ መስክ አድሮ የጠራ ምንጭ ውኃ ጠጥቶ በአምላኩ እንክብካቤ አድርጐ መጓዙን የሰው ልጅ አጥላልቶ ከስታለች ተርባ ነፍሱ ታውኳል ሥጋ መንፈሱ ይመለስ ሚወድ ይመለስ ሳይወድቅ ጉልበቱ ሳይፈር አዝ፦ ጌታ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል በስምህ ትዕዛዝ ስር ያድራል (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection