Song Lyrics

መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ

Dereje Kebede
Mengiste Semay
አዝ፦ ነገር ግን መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ ቢገድለኝም እንኳን እርሱን ጠብቃለሁ እርሱን ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ (2x) የሆነው ነገር ይምጣብኝ ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ ቢገድለኝ እንኳን ታግሼ ሕይወቴን በእጁ አኖራለሁ መድሃኒት ይሆንልኛል ነገሩ አይመረመርም እጠብቀዋለሁ ጌታን በጥቂቱ ዝዬ አልወድቅም አዝ፦ ነገር ግን መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ ቢገድለኝም እንኳን እርሱን ጠብቃለሁ እርሱን ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ (2x) በለስ እንኳን ባታፈራ የወይን ሃረግ ቢደርቅ ዝም ብዬ የጌታን ቀን በትዕግሥት ልጠብቅ የወራት ስራ ቢጐድል እርሾቼም ባያበሉኝ እግዚአብሔር ኃይሌ ይሆናል ጥሩ ሰዓት ሲወጣልኝ አዝ፦ ነገር ግን መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ ቢገድለኝም እንኳን እርሱን ጠብቃለሁ እርሱን ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ (2x) በውስጤ ስላደረው ተስፋ መንፈሱ አያሳፍረኝም እንደ ኢዮብ ሳያጽናናኝ እግዚአብሔር ከቶ አይተወኝም ከጋጣዬ የጠፉት ላሞች ነገ ይበራከታሉ ያላገጡብኝ ጠላቶች የአምላኬን ስራ ያያሉ አዝ፦ ነገር ግን መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ ቢገድለኝም እንኳን እርሱን ጠብቃለሁ እርሱን ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection