ኮረብታውን ወጥቼ እፎይ አልኩኝ ድንቅ የሆኑ ፍጥረታትን እያየሁኝ ብቻዬን ነኝ ለማለት አልደፈርኩም በዙሪያዬ አጫዋች አላጣሁም አዝ፦ ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ ቀስ እያልኩኝ ቀጠልኩኝ እርምጃዬን አቤት ወፎች ከበውኛል ዙሪያዬን ልዩ ልዩ ቀለም ለብሰው ሲጫወቱ ደስ ያሰኛል የአምላክ ጥበብ መሰረቱ አዝ፦ ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ ሽው እያለ በሚያዝናናኝ ነፋስ ደግሞ ሲወዛወዝ የ. (1) . አንገት ዘሞ አንዴ ቀና አንዴ ጐንበስ አቤት . (2) . እንዴት ሰራው ታላቅ ጌታስ ያሰኛል አዝ፦ ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ የአበቦቹ መዓዛ እያወደኝ ልዩ ቃና ለአካላቴ እየሰጠኝ በአምላክ እጆች በተሰሩት ተደንቄ ተመለስኩኝ ወደ ቤቴ ብዙ አውቄ አዝ፦ ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ