Song Lyrics

ዞር ብዬ ሳየው

Dereje Kebede
Hiwot Yishalenal
አጭር ጊዜ አይደለም ለረጅም ዘመናት በድካም በትግል ለአያሌ ዓመታት በመውደቅ መነሳት በውጊያ በጭንቀት እንደማያልፍ የለም [አለፈ ያ እሳት] 3x [ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን ማመን ይሳነኛል ኃይል ከየት አገኘሁ ለካ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ ሥሙን አከብራለሁ] መራራ አይታኘክ የመከራ እንጀራ የብቸኝነት ቤት እኔው ከእኔ ጋራ እንቅልፌን አጥቼ ብዙ ለሊት አልፏል ዛሬ ግን ታሪክ ነው [ተረት ነው ይወራል] x3 [ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን ማመን ይሳነኛል ኃይል ከየት አገኘሁ ለካ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ ሥሙን አከብራለሁ] የሕይወቴ ማብቂያ ዛሬ ነው ያልኩበት ዓይኖቼን ጨፍኜ ሞትን ያሰብኩበት ቀውጢው ሰዓት አልፎ ማየቴ ደንቆኛል ለካ ጌታ ወዶኝ [እጅ እግሬን ጠብቋል] 3x [ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን ማመን ይሳነኛል ኃይል ከየት አገኘሁ ለካ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ ሥሙን አከብራለሁ] ×2 የአብርሃም አምላክ በክንፉ ሸሸገኝ ለካ መጐዳቴን ተጐሳቁዬ አየኝ ያን ሁሉ ሻካራ ያን ሁሉ ጐርባጣ ጌታ ብርታት ሆነኝ [ችዬው እንድወጣ] ×3 [ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን ማመን ይሳነኛል ኃይል ከየት አገኘሁ ለካ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ [ሥሙን አከብራለሁ] ×3 ]
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection