Song Lyrics

ተመለስ ወደ ቤትህ

Dereje Kebede
Hiwot Yishalenal
[ተመለስ ወደ ቤትህ ወደ አባትህ ጉያ ስናይህ አነባን ሆነህ ከሕይወት ወድያ ታረቅ ከጌታ ጋር ዛሬ ነው ያንተ ቀን እንጠብቅሃለን] ×2 ውሸት ነው ቢጠራህ የዓለም ውበቷ ደርሰህ አይተኸዋል ከነማንነቷ ከስተህ ፊትህ ጠቁሮ ድካም በዝቶብሃል ና ወደ ኢየሱስ ወዝ ይሞላብሃል ይቅር መታለልህ የታለ ሰላምህ ያመዛዝን ልብህ [ተመለስ ወደ ቤትህ ወደ አባትህ ጉያ ስናይህ አነባን ሆነህ ከሕይወት ወድያ ታረቅ ከጌታ ጋር ዛሬ ነው ያንተ ቀን እንጠብቅሃለን] በመቅደሱ ሳለህ በግርማ ሞገስ ጌታን ስትወድስ በጠራ አንደበትህ ለብዙዎች መዳን ለብዙዎች ጽናት ነበርክ የጌታ ልጅ የምትሄድ በሙላት ከእግዚአብሔር ሸሽተህ ወዴት ትደርሳለህ አዝነህ ትቀራለህ [ተመለስ ወደ ቤትህ ወደ አባትህ ጉያ ስናይህ አነባን ሆነህ ከሕይወት ወድያ ታረቅ ከጌታ ጋር ዛሬ ነው ያንተ ቀን እንጠብቅሃለን] ምን ጎደለኝ ብለህ ጌታህን ለወጥከው "አተርፍ ባይ አጉዳይ" መሆንህ ለምን ነው ጀምበሯ ሳትጠልቅ ታረቅ ከአምላክ ጋር አትራቅ ከሕይወት አትሩጥ ወደ ሞት ዳር ወደ ቀድሞ ስፍራ ታረቅ ከአምላክ ጋራ ስማ ስትጠራ [ተመለስ ወደ ቤትህ ወደ አባትህ ጉያ ስናይህ አነባን ሆነህ ከሕይወት ወድያ ታረቅ ከጌታ ጋር ዛሬ ነው ያንተ ቀን እንጠብቅሃለን] ከለመድከው ጸጋ ከለመድከው ፍቅር ስትሸሽ ምንም ቢሆን ይልሃል ቅር ቅር በቀልን የማያውቅ ቡሩክ የእግዚአብሔር ልጅ ይቅር ይልሃል ና ከንቱ እድሜህን አትፍጅ [እኛም ደስ እንዲለን መመለስክን አይተን ዛሬን አንድ ብለን] ×3
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection