Song Lyrics

ፍጥረት አሸልቦት

Dereje Kebede
Hiwot Yishalenal
ጌታዬን መማፀን ያዋጣኛልና እንቅልፌን ልሰዋ ሲጠባ ንጋቱ ትንሽ ቢያስጎነጨኝ የምህረቱን ፅዋ ፊቱን መለስ አርጎ እንባዬን በዓይኑ ሲያይ ፈውስ ይሆንልኛል እሩሩህ ነው ፍፁም ነፍሴን ከአንድ ሁለቴ አድኖ ሰጥቶኛል ፍጥረት አሸልቦት እንቅልፍም ተጭኖት እኔ ግን ዓይኖቼ ገና አልተከደኑም የምህረቱን ደጃፍ እሻለሁ አሁንም (አሁንም) የሃጥአቴን መጠን ቆጥሮ ቢመዝነዉ ምህረት አይገባኝም በውድቅት ሌሊት የከበረ ስሙን መጥራት መብት የለኝም ነገር ግን ጌታዬ እንደሰው አይደለም ዘላለም የሚጥል አልተኛም ሌሊቱን ደጁን አንኳኳለሁ እጅ እግሬ እስከሚዝል ፍጥረት አሸልቦት እንቅልፍም ተጭኖት እኔ ግን ዓይኖቼ ገና አልተከደኑም የምህረቱን ደጃፍ እሻለሁ አሁንም (አሁንም) ተስፋ ያጣሁ መስዬ ማን ይቀበለኛል ወዴት እሄዳለሁ ግድ ያለው ለነፍሴ ኢየሱስ ነዉና ስሙን እጠራለሁ ዶሮ ሲጮህ ያኔ እጁ ይዳስሰኛል ፍቅር ግድ ይለዋል መድሃኒት የሆነኝ እድሜዬን ቀጣዩ መቼ ያስችለዋል [ፍጥረት አሸልቦት እንቅልፍም ተጭኖት እኔ ግን ዓይኖቼ ገና አልተከደኑም የምህረቱን ደጃፍ እሻለሁ አሁንም (አሁንም)] ×2
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection