Song Lyrics

ተላላ ነው ማዳኑን ቸል የሚል

Dereje Kebede
Hiwot Yishalenal
በዚህ ክፉ ዘመን በሚያጫክን ፍጥረት ሲተራመስ ነፍሱን ሊያድን እሮሮውን አዳማጭ አጥቶ ህዝቡ አጥፍቶ ሊጠፋ ሆኖ አሳቡ ደቂቃው መራራ ቀኑ ረጅም "በድብ የመሸነፍ" ለኑሮ አይጥም [ተላላ ነው ማዳኑን ቸል የሚል ትልቅ ትንሽ ይሻላል ቢያስተውል የእጁን አልማዝ አሽቀንጥሮ ባይጥል] ×2 የጣር ጩኸት በዝቶ በየለቱ ቢላዋውን ሲስል ልጅ በአባቱ ጥላውን ሲሸሸው ሰው ደንብሮ መተማመን ጠፍቶ "የቆቅ ኑሮ" ፍጥረት ተተራምሶ እየሄደ ነው ምሽጋችን እንቆይ ውጪው ሞት ነው [ተላላ ነው ማዳኑን ቸል የሚል ትልቅ ትንሽ ይሻላል ቢያስተውል የእጁን አልማዝ አሽቀንጥሮ ባይጥል] ×2 ዋስትና የሚሰጥ አንዳች የለም ምድር ተጨናንቋል ፍጥረት ዓለም በሽታና ረሃብ ዘውድ ጭነው ይህን ክፉ ዘመን እያየነው ኢየሱስ እያለን ልንድንበት እግራችን ሲቻኮል ወደ መቅሰፍት [ተላላ ነው ማዳኑን ቸል የሚል ትልቅ ትንሽ ይሻላል ቢያስተውል የእጁን አልማዝ አሽቀንጥሮ ባይጥል] ×2 ዋስትና የሚሰጥ አንዳች የለም ምድር ተጨናንቋል ፍጥረት ዓለም በሽታና ረሃብ ዘውድ ጭነው ይህን ክፉ ዘመን እያየነው ኢየሱስ እያለን ልንድንበት እግራችን ሲቻኮል ወደ መቅሰፍት [ተላላ ነው ማዳኑን ቸል የሚል ትልቅ ትንሽ ይሻላል ቢያስተውል የእጁን አልማዝ አሽቀንጥሮ ባይጥል] ×2
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection