ያለው በዙሪያችን ያጓጓናል የምንቀምሰዉ ለአፋችን ጣፍጦናል የምናየዉ ውበት ማርኮታል ልባችን (ልባችን) ግን ምንም አይበልጥም ከውድ ነፍሳችን (ከውድ ነፍሳችን) [ሕይወት ይሻለናል ወዳጄ ሕይወት ይሻለናል ዓለምን ብናተርፍና ነፍሳችንን ብንጥል ምን ይጠቅመናል ይልቅ ሕይወት ይሻለናል] ×2 ዘላለማዊውን አለውጥ በአላፊ ዛሬ ታይቶ ነገ ደግሞ ጠፊ ይልቅ ብልህ ሆነን እንጽና ለሕይወት (ለሕይወት) ይሻላል ከእርሱ ጋር ዘላለም መሰንበት (ዘላለም መሰንበት) [ሕይወት ይሻለናል ወዳጄ ሕይወት ይሻለናል ዓለምን ብናተርፍና ነፍሳችንን ብንጥል ምን ይጠቅመናል ይልቅ ሕይወት ይሻለናል] ×2 ብልህ ሰው ለነገ ይሰንቃል ያለመሰናከል መንገዱን ይዘልቃል እኔም አንተም ሆነን ተያይዘን ዘልቀን (ዘልቀን) ሞትን ወደኋላ እንጥለዋለን (እንጥለዋለን) [ሕይወት ይሻለናል ወዳጄ ሕይወት ይሻለናል ዓለምን ብናተርፍና ነፍሳችንን ብንጥል ምን ይጠቅመናል ይልቅ ሕይወት ይሻለናል] ×2