Song Lyrics

ለእኛ ግን መጠለያችን

Dereje Kebede
Hiwot Yishalenal
እንግዳ ነገር እንሰማለን አዲስ ነገር እናያለን ወየው እያልን እንሰጋለን ጠባቂው አምላክ ከሌለን ለእኛ ግን መጠለያችን እግዚአብሔር ነውና የዋርካ ጥላችን እግዚአብሔር [ወሬው ሁሉ የሚያስፈራ የሚሆነው በምድር ዙሪያ እየከፋ ሲሄድ ጊዜው መሸሸጊያ ኢየሱስ ነው] ×2 ጦርነት በዝቶ በዙሪያችን ርሃብ ፀንቶብን በዓለማችን ጥማት አቃጥሎን አሮ አፋችን ኢየሱስ ብቻ ነው ተስፋችን ለእኛ ግን መጠለያችን እግዚአብሔር ነውና የዋርካ ጥላችን እግዚአብሔር [ወሬው ሁሉ የሚያስፈራ የሚሆነው በምድር ዙሪያ እየከፋ ሲሄድ ጊዜው መሸሸጊያ ኢየሱስ ነው] ×2 ሞትን ቁም ነገር ማን ይለዋል ሰው እንደ እንሰሳ መንገድ ወድቋል የእሳት ቃጠሎ የአውሎ ነፋስ በጎርፍ በጦርነት ጥፋት ለእኛ ግን መጠለያችን እግዚአብሔር ነውና የዋርካ ጥላችን እግዚአብሔር [ወሬው ሁሉ የሚያስፈራ የሚሆነው በምድር ዙሪያ እየከፋ ሲሄድ ጊዜው መሸሸጊያ ኢየሱስ ነው] ×2 ወላጅ ልጆቹን ክዶ ሲሸሽ መጠጊያ ላጣ ኑሮ ሲመሽ ከቦን ምስቅልቅል ያለው ዓለም አዳኝ ያለ ኢየሱስ የለም ለእኛ ግን መጠለያችን እግዚአብሔር ነውና የዋርካ ጥላችን እግዚአብሔር [ወሬው ሁሉ የሚያስፈራ የሚሆነው በምድር ዙሪያ እየከፋ ሲሄድ ጊዜው መሸሸጊያ ኢየሱስ ነው] ×2 ለእኛ ግን መጠለያችን እግዚአብሔር ነውና የዋርካ ጥላችን እግዚአብሔር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection