ከትንሽነቴ ሰልፍ ይበዛብኛል እንቅፋቱ በዝቶ ያቆሳስለኛል እፎይ የምልበት የእረፍቴ ሰዓት [ ለዓይኔ አይታየኝም ለአዕላፍ ቀናት ] ×2 ጌታ ሆይ ምክንያቱን አላውቅም መስቀሌ ብዙ ነው [ ትከሻዬን አስፋ ችዬ እንድሸከመው ] ×2 በግፈኞችም እጅ ወድቄ አልቅሻለሁ መንገዴን አጥብበው ብዙ ታግያለሁ ስጋዬ በህመም ደቆ ተንጋልዬ [ ቀናት ተፈራርቀው ሳለሁኝ በአልጋዬ ]×2 ጌታ ሆይ ምክንያቱን አላውቅም መስቀሌ ብዙ ነው [ ትከሻዬን አስፋ ችዬ እንድሸከመው ] ×2 ፈቃድህ ከሆነ ሀሞት እቀምሳለሁ የሚያስችል ኃይልህን እከናነባለሁ የማታ የማታ ባለድል እሆናለሁ [ የጸና ስምህን በእምነት እጠራለሁ ] ×2 ጌታ ሆይ ምክንያቱን አላውቅም መስቀሌ ብዙ ነው [ ትከሻዬን አስፋ ችዬ እንድሸከመው ] ×2 ሰገነት ላይ በቅሎ እንደ ደረቀ ሳር ፈታኜ ይጠውልግ ይገፍተር ወደ ዳር ብሩህ ቀን የደስታ አዲስ ቀን አያለሁ [ አንተን ተደግፌ ድሌን አውጃለሁ ] ×2 ጌታ ሆይ ምክንያቱን አላውቅም መስቀሌ ብዙ ነው [ ትከሻዬን አስፋ ችዬ እንድሸከመው ] ×2