የማመልከው አምላክ ሳይንስ አይጨብጠው የፊደላት ብዛት እውቀት አይገምተው መንፈሳዊ ዓይኖች ተከፍተው ካላዩት ቃሉ ሞኝነት ነው አውቀናል ለሚሉት [ሞኝ ነው አልተማረም አሉኝ ለእግዚአብሔር አድሬለት ቢያዩኝ ትርፌን እና ጥቅሜን ባለማወቃቸው እኔ አዘንኩላቸው] (×2) [ይልቅስ ሳይጨልም መዝጊያው ሳይቆለፍ የሰው ልጅ ይመለስ ለሚጠፋው ዓለም ጉልበትን ከማፍሰስ] (×2) የሚጠፋ ጥሪት ማከማቸት ትቼ ዘላለማዊውን ለማግኘት ተግቼ ጌታዬን የሙጥኝ ብዬ መወሰኔ ከአዋቂዎች በላይ አልሆንኩም ወይ እኔ? [ሞኝ ነው አልተማረም አሉኝ ለእግዚአብሔር አድሬለት ቢያዩኝ ትርፌን እና ጥቅሜን ባለማወቃቸው እኔ አዘንኩላቸው] (×2) [ይልቅስ ሳይጨልም መዝጊያው ሳይቆለፍ የሰው ልጅ ይመለስ ለሚጠፋው ዓለም ጉልበትን ከማፍሰስ] (×2) ምድርና ሰማይን ያበጀው ፈጣሪ አይመረመርም ገብቶ ላብራቶሪይ ቁጥርን ከቁጥር ጋር ሲያጋጩ ቢኖሩ አያዩትም ጌታን ሩቅ ነው ሀገሩ [ሞኝ ነው አልተማረም አሉኝ ለእግዚአብሔር አድሬለት ቢያዩኝ ትርፌን እና ጥቅሜን ባለማወቃቸው እኔ አዘንኩላቸው] (×2) [ይልቅስ ሳይጨልም መዝጊያው ሳይቆለፍ የሰው ልጅ ይመለስ ለሚጠፋው ዓለም ጉልበትን ከማፍሰስ] (×2) ሰዓቱ ገና አለ ጊዜያችን አልገባም እግዚአብሔር ያን ደጁን በሰው ልጅ አልዘጋም ከማንቀላፋቱ ነቅቶ ለታረመ ብርሃን ነው ገና ዛሬ መች ጨለመ [ሞኝ ነው አልተማረም አሉኝ ለእግዚአብሔር አድሬለት ቢያዩኝ ትርፌን እና ጥቅሜን ባለማወቃቸው እኔ አዘንኩላቸው] (×2) [ይልቅስ ሳይጨልም መዝጊያው ሳይቆለፍ የሰው ልጅ ይመለስ ለሚጠፋው ዓለም ጉልበትን ከማፍሰስ] (×2)