Song Lyrics

ዓይኔን አንስቼ

Dereje Kebede
Hiwot Yishalenal
ለብዙ ዘመናት ሽንጤን ገትሬያለሁ ስሰበር ስደማ አላቅሜ እያየሁ አዬ አዬ ዬ ዬ ዬ ከእግዚአብሔር ጋር ውጊያ ምንም አልጠቀመኝ እጆቼን አነሳሁ አዝኖ ቢማርከኝ አዬ አዬ ዬ ዬ ዬ ዓይኔን አንስቼ ጨፍኜ እንዳላይህ በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ የምድረበዳው ኑሮ ይበቃኛል እጆቼን ላንሳ ዛሬስ ማርከኸኛል ተማርኬያለሁ ዛሬስ ማርከኸኛል ተማርኬያለሁ በምስራቅ ሂድ ሲለኝ ምዕራብን ስከተል የሰጠኝን ክልል አጥሩን ጥሼ ስዘል አዬ አዬ ዬ ዬ ዬ ብዙ ተገጣጠብኩ ጠባሳ ብቻ ነኝ ይቅርታው ብዙ ነው ምሕረቱ ያስታመኝ አዬ አዬ ዬ ዬ ዬ አይኔን አንስቼ ጨፍኜ እንዳላይህ በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ የምድረበዳው ኑሮ ይበቃኛል እጆቼን ላንሳ ዛሬስ ማርከኸኛል ተማርኬያለሁ ዛሬስ ማርከኸኛል ተማርኬያለሁ ለዘላለም ቁጡ እንዳይሆን በኔላይ እግዚአብሔር በልጁ ቀድሶኝ ከሰማይ አዬ አዬ ዬ ዬ ዬ እግሮቹ ስር ሆኜ ትዕዛዙን ፈጽሜ ልኖር ነው ምኞቴ በቀረው ዘመኔ አዬ አዬ ዬ ዬ ዬ ዓይኔን አንስቼ ጨፍኜ እንዳላይህ በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ የምድረበዳው ኑሮ ይበቃኛል እጆቼን ላንሳ ዛሬስ ማርከኸኛል ተማርኬያለሁ ዛሬስ ማርከኸኛል ተማርኬያለሁ አዳከመኝ ትግል ከማልችለው ጋራ አቅሜን አለማወቅ አጉል ስንጠራራ አዬ አዬ ዬ ዬ ዬ ኤልሻዳዩ ከላይ ወደታች እያየኝ ትጥቄ ላልቶ ስወድቅ አዝኖ ሰበሰበኝ አዬ አዬ ዬ ዬ ዬ ዓይኔን አንስቼ ጨፍኜ እንዳላይህ በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ የምድረበዳው ኑሮ ይበቃኛል እጆቼን ላንሳ ዛሬስ ማርከኸኛል ተማርኬያለሁ [ዛሬስ ማርከኸኛል ተማርኬያለሁ] (×2)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection