አዝ፦ ያምላኬ ቃል አያረጅም የኢየሱስ ቃል አያረጅም ዘለዓለም ይኖራል እያበራ ከሚያምኑት ጋራ (2x) ተስፋ ስቆርጥ ያጽናናኛል አቅፎ ደግፎ ያኖረኛል በደሙ አጥቦ አንጽቶኛል ኮብልዬ እንዳልሄድ ይጠብቀናል አዝ፦ ያምላኬ ቃል አያረጅም የኢየሱስ ቃል አያረጅም ዘለዓለም ይኖራል እያበራ ከሚያምኑት ጋራ (2x) በዓለም ጉዞዬ ይደግፈኛል ፍፁም ላይተወኝ ተስፋ ሰጥቶኛል አልተወውም አይተወኝም የኢየሱሴ ነኝ እስከዘለዓለም አዝ፦ ያምላኬ ቃል አያረጅም የኢየሱስ ቃል አያረጅም ዘለዓለም ይኖራል እያበራ ከሚያምኑት ጋራ (2x) ሥጋዬ ደክሞ ነፍሴ ተጨንቃ ስታንቀላፋ የአምላኬ ቃል ያነቃኛል በሰጠኝ ተስፋ ልጁ ሆኛለሁ ዳግም ወልዶኛል ኃጢአቴን ሁሉ ደምስሶልኛል ጌታዬ አቅፎኝ በእርሱ ስር ካለሁ ብርሃን እያየሁ እጓዛለሁ አዝ፦ ያምላኬ ቃል አያረጅም የኢየሱስ ቃል አያረጅም ዘለዓለም ይኖራል እያበራ ከሚያምኑት ጋራ (2x) ከሚያምኑት ጋራ