አዝ፦ ተራመድ በርታ በርታ ጉዞህንም ቀጥል ሕይወትንም አድን የመከራ ጉም በላይ ቢያንዣብብ አለና ኢየሱስ ፍፁም አታስብ ቢመስልህ ጉዞ ፍፁም ተራራ ደጋፊ አለህ ፍፁም አትፍራ አዝ፦ ተራመድ በርታ በርታ ጉዞህንም ቀጥል ሕይወትህንም አድን በኃጢአት ቁስል ብትማቅቅም በስሙ ካመንክ ፍፁም አትወድቅም ስለሚመለስ ጌታ ከሰማይ መብራትህ ይብራ ለዓለምም ይታይ አዝ፦ ተራመድ በርታ በርታ ጉዞህንም ቀጥል ሕይወትህንም አድን አትሞኝ ከቶ በዓለም ደስታ ስለማታገኝ ለሕይወትህ ፋታ መቅረዝህ ይብራ ቁም ተዘጋጅተህ ጌታ ሲመለስ ትነጠቃለህ አዝ፦ ተራመድ በርታ በርታ ጉዞህንም ቀጥል ሕይወትህንም አድን ቋሚ ጓደኛ ስላለህ ኢየሱስ በእምነት ተጋደል በተስፋ ገስግስ ዓለምን አትይ ማብለጭለጯንም ተስፋ ከመቁረጥ አታድንህም አዝ፦ ተራመድ በርታ በርታ ጉዞህንም ቀጥል ሕይወትህንም አድን (2x)