አዝ፦ ጠፊዋን ዓለም ተለይቼ ለዘለዓለም ተሰናብቼ የሚሞተው ተለውጦ የማይሞተውን ኢየሱስን ለብሶ (2x) ከጌታ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ ዓለምንና ሃሳቧን ትቻለሁ ከላይ የሚመጣውን እጠብቃለሁ በቅጽበት ወደእርሱ እነጠቃለሁ አዝ፦ ጠፊዋን ዓለም ተለይቼ ለዘለዓለም ተሰናብቼ የሚሞተው ተለውጦ የማይሞተውን ኢየሱስን ለብሶ (2x) በጉጉት ናፍቆት ፊቱን ሳይ ኢየሱስን ሳገኝ በላይ በሰማይ ፊቱን ስመለከት እምባዬን ሲያይ እየዳሰሰ ዓይኔን ያብሳል አዝ፦ ጠፊዋን ዓለም ተለይቼ ለዘለዓለም ተሰናብቼ የሚሞተው ተለውጦ የማይሞተውን ኢየሱስን ለብሶ ጌታ መምጣቱ ያሳውጃል በደጅ እንደቆመ ሕይወቴም ያውቃል ቀኑ እንደደረሰ ተረድጄ ተጨማሪ ዘይት ልግዛ ተግቼ አዝ፦ ጠፊዋን ዓለም ተለይቼ ለዘለዓለም ተሰናብቼ የሚሞተው ተለውጦ የማይሞተውን ኢየሱስን ለብሶ (2x)