የዓለም መራቀቅ እኔን አይገደኝም የጠላት ድንፋታም አያስጨንቀኝም አምላኬን አውቃለሁ ፍፁም የለም ቢሉ እኔስ አለ እላለሁ ተናግሮኛል ቃሉ አዝ፦ ነፍሴን ለሞት ሽጬ አለሁኝ አልልም ላያዛልቅ ኑሮ አምላኬን አልክድም እኔ እኔነቴን እስካላዘዝኩበት የሚያዝበት አለ ሌላ ባለንብረት ይህን ክቡር ገላ በዋዛ አላየውም የፈጠረኝንም አምላኬን አልክድም አዝ፦ ነፍሴን ለሞት ሽጬ አለሁኝ አልልም ላያዛልቅ ኑሮ አምላኬን አልክድም ገንዘብ ነው ጌጣጌጥ የትኛው ነው ትርፉ ከአምላክ ተነጥሎ በዓለም ውስጥ መክነፉ ሁሉም ሥጋ ለባሽ ወደ አፈር ከሄደ ዋጋው የላቀ ነው አምላክን ያልካደ አዝ፦ ነፍሴን ለሞት ሽጬ አለሁኝ አልልም ላያዛልቅ ኑሮ አምላኬን አልክድም