እግዚአብሔር ነገሠ ክብር ለበሰ ታጠቀ ኃይልንም ለበሰ ዓለምን አጸናት አቆማት ምሕረቱም ድንቅ ዘለዓለማዊ አዝ፦ ክብር ይገባሃል የእኛ አምላክ (2x) ዙፋንም ምሥጋናም ለአንተ ነው (2x) ክብር ሃሌሉያ (3x) ክብር ሃሌሉያ ዘለዓለማዊ አምላክ አንተ ነህ ዝግጁ ነው ከጥንት ዙፋንህ ወንዞች ከፍ አደረጉ ድምጻቸውን ተራሮች ሰጡህ ክብርን አዝ፦ ክብር ይገባሃል የእኛ አምላክ (2x) ዙፋንም ምሥጋናም ለአንተ ነው (2x) ክብር ሃሌሉያ (3x) ክብር ሃሌሉያ ከብዙ ውሃዎች ድምጽ ይልቅ ከታላቅ ሞገድም ድምጽ ይልቅ ጌታችን አንተ ነህ ኃያል ድንቅ ምስክር ታማኝ አንተ ታላቅ አዝ፦ ክብር ይገባሃል የእኛ አምላክ (2x) ዙፋንም ምሥጋናም ለአንተ ነው (2x) ክብር ሃሌሉያ (3x) ክብር ሃሌሉያ