አክሊሌን በደምህ ልሸሽገው የሰው ልጅ ጠላት ሰይጣን እንዳይሰርቀው መፈታተኑን አላቋረጠም አንተ እስክትመጣ በክብር ወደዚች ዓለም ከባሕር ሞገድ ከአየር ነጐድጓድ በሚበልጥ ኃይልህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ አጥበኸኝ እኔን ድኛለሁ ጌታ ለአክሊልህ ያብቃኝ ኢየሱስ እንዳልረታ ጠበቃዬና አክሊሌን ይዘህ በመርከብህ ውስጥ ልግባ እኔም እንደ ኖህ ጐልማሳነቴን ሩጫዬን በቃኝ አክሊሌን ከአንተ ኢየሱስ ለመውሰድ አብቃኝ ከባሕር ሞገድ ከአየር ነጐድጓድ በሚበልጥ ኃይልህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ አጥበኸኝ እኔን ድኛለሁ ጌታ ላክሊልህ ያብቃኝ ኢየሱስ እንዳልረታ