Song Lyrics

ካልባረከኝ

Dereje Kebede
Collection 1
ለብቻዬ ልኖር ፈቃድህ ከሆነ ሌላው አይገደኝም ሕይወቴ ከዳኔ ሲዖል እስከንጋት . (1) . ስደደኝ ጌታ ሆይ ሕይወቴን ባርክና አዝ፦ ካልባረከኝ አለቅህም (2x) ካልባረከኝ አለቅህም (2x) ከመምበርከክ ብዛት በጸሎት ትግል ፈቃድህ ከሆነ ጉልበቴ ይዛል እያነከስኩ ይሁን እከተልሃለሁ እጅህን ዘርጋብኝ በረከት እሻለሁ አዝ፦ ካልባረከኝ አለቅህም (2x) ሊነጋ ሲጀምር ሰማዩም ሲቀላ ወደዚህ እሄዳለሁ ነፍሴ እንዲህ ዝላ ሕይወቴን ብቻ ባርክ ሌላ አልመኝም ሥም እንደው ቀሪ ነው ሥም አያድነኝም አዝ፦ ካልባረከኝ አለቅህም (2x) ካልባረከኝ አለቅህም (2x) እንደ ያዕቆብ ዛሬ ጩኸቴን ስማና ስደደኝ ጌታ ሆይ ሕይወቴን ባርክና ፈቃድህ ከፎነ ስሜንም ለውጠው ሰው እንዳለው ሳይሆን አንተ እንደ ወደድከው አዝ፦ ካልባረከኝ አለቅህም (2x) ካልባረከኝ አለቅህም (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection