Song Lyrics

እኔን ጌታ ሆይ

Dereje Kebede
Collection 1
ቃልህን ለማንበብ ዓይኔ ታወረ እንዳልጸልይ ጉልበቴ ታሰረ አንተን እንዳላስብ አዕምሮዬ ዛለ እግሬም ወደ ጥፋት ኮበለለ እኔን ጌታ ሆይ ድካም ይዞኛል ድምጼንም ላሰማህ አቅቶኛል ወድቄያለሁኝ ጌታ ሆይ አንሳኝ እባክህ ሕይወቴን ለውጥልኝ ጠፋሁኝ ጌታ ካልደረስክልኝ ዓለም እንደ ጐርፍ አነከባለለኝ ከኃጢአት ባሕር ልሰምጥ ነውና ጌታ ቆይ እባክህ እጄን ያዘኝ መች ጨቀንክ ጌታ በእኔ በልጅህ አውቃለሁኝና ጉድለቴን ጌታ ሆይ አሁን ኃጢአቴን ማረኝ የምመራበትን ብርሃን ስጠኝ አየሁ ጌታዬን ወዲህ ስመጣ እኔንም ከጥፋት ሊያወጣ እጁን ላከልኝ ፍፁም አዳነኝ ከእንግዲህስ ከጌታዬ ጋር ነኝ ፍፁም ቸል አልልም እርሱን ስከተል እኔኑን ለመውሰድ ስለሚያስብ መስቀሉ ለእኔ ቢከብደኝ እንኳን ፍፁም ለመሸከም አልቦዝንም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection