Song Lyrics

እንዴት ድንቅ አምላክ ነው

Dereje Kebede
Collection 1
የደን ልማቱ የገደል ስርገቱ የወንዝ እርዝመቱ የቀላይ ውበቱ የቆንጆ ገጽታው የቦታ ከፍታው የባሕር ጥልቀቱ የሜዳ ስፋቱ እኛ ምናመልከው መሠረቱ አዝ፦ እንዴት ድንቅ አምላክ ነው እኛ ምናመልከው እንደምን ኃያል ነው እኛ ምንሰግድለት የኃይል ሁሉ ጉልበት የፍጥረት መሠረት የሽቶ መዓዛው የሙዚቃ ቃናው የለምለም እርካታው የመዝናኛ ቦታው የመፋቅር ወዙ የትዳር ማገዙ የፍጥረት ድምቀቱ የሰማይ ርቀቱ እኛ ምናመልከው መሠረቱ አዝ፦ እንዴት ድንቅ አምላክ ነው እኛ ምናመልከው እንደምን ኃያል ነው እኛ ምንሰግድለት የኃይል ሁሉ ጉልበት የፍጥረት መሠረት የአበቦች ፍካታ የወፎች ጫጫታ የቀለም መዋሃድ የሰው ልጅ መዋደድ የእምነት እርካታ ሰላምና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection