Song Lyrics

ግሩም ነው ድንቅ ነው

Dereje Kebede
Collection 1
አዝ፦ ግሩም ነው ድንቅ ነው ጌታ ሲሰራ አየነው ምርኮው ላይ ግርማው ሲያበራ የኃጢአት መጋረጃን በደሙ ቀደደ ከሳሻችን አፍሮ ወድቆ ሰገደ ይከሰን የነበረው የእዳ ጽሕፈት በደሙ ተደምስሷል በጌታ ኢየሱስ ሞት ቀንበራችን ተሰብሮ አርነት ወጥተናል ጠላቶች የነበርነው በፀጋው ቀርበናል አዝ፦ ግሩም ነው ድንቅ ነው ጌታ ሲሰራ አየነው ምርኮው ላይ ግርማው ሲያበራ የኃጢአት መጋረጃን በደሙ ቀደደ ከሳሻችን አፍሮ ወድቆ ሰገደ ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን በጌታ ኢየሱስ ሥራ እግዚአብሔር ጠራን ተስፋችን ያከተመ ደካሞች ሳለን በዘመኑ ፍፃሜ በልጁ ዋጀን አዝ፦ ግሩም ነው ድንቅ ነው ጌታ ሲሰራ አየነው ምርኮው ላይ ግርማው ሲያበራ የኃጢአት መጋረጃን በደሙ ቀደደ ከሳሻችን አፍሮ ወድቆ ሰገደ አእላፋት መላዕክት አገልጋይ ሳያንሰው ስለጠፋው የሰው ልጅ አንድ ልጁን ሰዋው በኃጢአት ረግረግ ውስጥ ሰጥመን ለጠፋነው ሊታደገን ወደደ ጭንቀታችን ተሰማው አዝ፦ ግሩም ነው ድንቅ ነው ጌታ ሲሰራ አየነው ምርኮው ላይ ግርማው ሲያበራ የኃጢአት መጋረጃን በደሙ ቀደደ ከሳሻችን አፍሮ ወድቆ ሰገደ መንገድ ተዘጋጀልን ግዛቱ ልንገባ የከበደን ቀንበር ሆኗል እንደ ገለባ እንራመዳለን ሸክም ቀሎናልና ዕረፍትን ስላገኘን ሆነን በምሥጋና አዝ፦ ግሩም ነው ድንቅ ነው ጌታ ሲሰራ አየነው ምርኮው ላይ ግርማው ሲያበራ የኃጢአት መጋረጃን በደሙ ቀደደ ከሳሻችን አፍሮ ወድቆ ሰገደ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection