አዝ፦ ጌታ ቅደምልኝ በኑሮዬ ሁሉ የአንተ ስለሆነ በመከራ ድሉ (2x) ጌታን የሚያስቀድም በኑሮው በቤቱ አቅፎ እንደ ደገፈው እንደ እናት አባቱ ያ ነው የአምላክ ወዳጅ ክብሩን የማይፈልግ በክፉ በደጉ ከቶ ማይበረግግ አዝ፦ ጌታ ቅደምልኝ በኑሮዬ ሁሉ የአንተ ስለሆነ በመከራ ድሉ (2x) በትዕግሥት ጠብቁ አምላክ ይቅደም የሚል እራሱን በውርደት ከመስቀሉ ሚጥል ያ ነው ያምላክ ወዳጅ ምኞቱን ያሟላ ለያዘው ቁም ነገር ከቶ የማይላላ አዝ፦ ጌታ ቅደምልኝ በኑሮዬ ሁሉ የአንተ ስለሆነ በመከራ ድሉ (2x) ጌታ እንድቀድምልህ በኑሮው መከራ በእምባው እየታጀበ ለመዝሙር ሲጠራ ያ ነው የአምላክ ወዳጅ ክብሩን የሰቀለ ያጋንንትን ሥልጣን በእምባው ያቃጠለ አዝ፦ ጌታ ቅደምልኝ በኑሮዬ ሁሉ የአንተ ስለሆነ በመከራ ድሉ (2x)