Song Lyrics

ወንዙ ከፊት ሲታይህ

Dereje Kebede
Collection 1
አዝ፦ ወንዙ ከፊት ሲታይህ ቢመስልህ የሚውጥህ ታምነህ ጉዞህን ቀጥል ጌታ ይመራሃል የማዕበሉ ጌታ ቀድሞሃል ተከተለኝ አይዞህ ይልሃል ቀና ነው መንገዱ ተጽናና የናዝሬቱ ኢየሱስ አለና አዝ፦ ወንዙ ከፊት ሲታይህ ቢመስልህ የሚውጥህ ታምነህ ጉዞህን ቀጥል ጌታ ይመራሃል ባሕሩ አፍ ለአፍ ሞልቶ ወጀብ ሲያናውጠው በርትቶ ሰንጥቀህ ማለፍን ብትፈራ ቶሎ ብለህ ጌታህን ጥራ አዝ፦ ወንዙ ከፊት ሲታይህ ቢመስልህ የሚውጥህ ታምነህ ጉዞህን ቀጥል ጌታ ይመራሃል ሁሉንም በቃሉ ያዘዋል ፍጥረትም ለእርሱ ይታዘዛል ሁሉን ቻይ ጌታ አለ ከፊትህ ጠላት ሲረፈረፍ ታያለህ አዝ፦ ወንዙ ከፊት ሲታይህ ቢመስልህ የሚውጥህ ታምነህ ጉዞህን ቀጥል ጌታ ይመራሃል በባሕሩ ጉዞ ብትዝልም አይዞህ መንገድ ላይ አትቀርም ጌታህ አጠገብህ አለና እርዳኝ በለው ጠጋ በልና አዝ፦ ወንዙ ከፊት ሲታይህ ቢመስልህ የሚውጥህ ታምነህ ጉዞህን ቀጥል ጌታ ይመራሃል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection