Song Lyrics

አዎን ያያል

Dereje Kebede
Collection 1
ያየኛል ወይ ልቤ ሲጨነቅ ለነፍሴ ሰላም ስሻ ሸክም ሲከብደኝ ስንገላታ መንገዴ ሁሉ ስደክም አዝ፦ አዎን ያያል ይረዳኛል ሳዝን ልቡ ይነካል በመንገዴ ሁሉ ፈተና ሲገጥመኝ ኢየሱስ ይረዳኛል ያየኛል ወይ ቀኑ ሲጨልም ፍርሃትም እኔን ሲከበኝ ተስፋ ቆርጬ ፍፁም ስደክም አምላኬ በቅርብ አለ ወይ አዝ፦ አዎን ያያል ይረዳኛል ሳዝን ልቡ ይነካል በመንገዴ ሁሉ ፈተና ሲገጥመኝ ኢየሱስ ይረዳኛል ያየኛል ወይ ኃይሌ ሲከዳኝ ችግር ልቋቋም ሳልችል ሳዝን ስተክዝ እምባዬም ሲፈስ አምላኬ በእርግጥ አለ ወይ አዝ፦ አዎን ያያል ይረዳኛል ሳዝን ልቡ ይነካል በመንገዴ ሁሉ ፈተና ሲገጥመኝ ኢየሱስ ይረዳኛል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection