አንድ ነገር በልቤ ሆነ ኢየሱስ ሲያድነኝ (2x) ሕይወቴም በፍቅሩ ጋለ ክብር ክብር ለስሙ አምላኬ በዚያ መስቀል ላይ በቀራኒዮ (2x) ለእኔ መከራውን አየ ደሙም እኔን አነጻኝ ግንባርህ በሾህ ተበሳ መራራን ጠጣ (2x) ጐንህም በጦር ተወጋ ስለእኔ ኃጢአት ብለህ የደም ላብም አጠለቀህ በጸሎት ሜዳ (2x) አህዛብም ቀለዱብህ መቱህ ተፉብህ ጌታ