ክንድህ ይበርታ በጠላትህ በር ሥራቸው ይፍረስ ይድቀቅ ይሰበር ሃሌሉያ ስምህ ይለምልም ዙፋንህ ይጽና ለባሪያህ በጐ ውለሃልና ሃሌሉያ አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው አምላኬ እረኛዬ ነው (2x) ውዳሴን ከአፌ አንተን ከልቤ ከቶም አይጠፋ ብኖር ተርቤ ሃሌሉያ የቅርብ ወዳጄ የጦር አዝማቼ ብቻ አትለየኝ ብቆይ ታክቼ ሃሌሉያ አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው አምላኬ እረኛዬ ነው (2x) ብቆም ብቀመጥ ብሄድ ብተኛ አምላኬ አንተ ነህ የእኔ ጓደኛ ሃሌሉያ ፅልመት ሲመጣ የመከራ ጉም አንተን ጠርቼ እኔ አላፈርኩኝ ሃሌሉያ አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው አምላኬ እረኛዬ ነው (2x) ሕመም ሞትህን ሥጋዬ ለብሶ ይዋረድ ይለፍ ጽዋህን ቀምሶ ሃሌሉያ የጻድቁን ሞት ነፍሴ ተጠምታ ትጥገብ አትፈር ስምህን ጠርታ ሃሌሉያ አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው አምላኬ እረኛዬ ነው (2x)