1. የዕውቀት ራስ የጥበብ ጌታ ምንም ቢፈተን የማይረታ በሰው አእምሮ አይገመትም ወርዱም ስፋቱም አይዘልቅም አዝ፦ አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ አመልካለሁ በማንም የማይረታ አመልካለሁ ግንበኞች የናቁትን አመልካለሁ የማዕዘን ዕራስን 2. ፍቅሩን አይቼ ቀምሸዋለሁ ፍጹም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ በመከራዬ እርሱ እየገባ ይጋፈጠዋል እንዳልረታ አዝ፦ አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ አመልካለሁ በማንም የማይረታ አመልካለሁ ግንበኞች የናቁትን አመልካለሁ የማዕዘን ዕራስን 3. ጥፋቴን ሁሉ በፍቅር እያየ ያሳልፈኛል ልጄ እያለ ከሁሉም በፊት ፍቅሩ ሰብሮኛል በመስቀሉ ላይ ነፍሱን ሰጥቶኛል አዝ፦ አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ አመልካለሁ በማንም የማይረታ አመልካለሁ ግንበኞች የናቁትን አመልካለሁ የማዕዘን ዕራስን 4. ከእርሱ ሌላ ወዳጅ የለኝም እንደርሱ የሚሆን ከቶ አላገኝም የውስጥ ችግሬን ሳልነግረው ያውቃል ለእኔ ሲከብደኝ ይሸከመዋል አዝ፦ አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ አመልካለሁ በማንም የማይረታ አመልካለሁ ግንበኞች የናቁትን አመልካለሁ የማዕዘን ዕራስን