በቃ አልፈልግም ልቤን ውሰደው አዕምሮዬን ግዛው ላአንተው አድርገው ዝም ልበልና ኃይልህን ልመልከት ሌላው ሃሣቤ ይብቃ ይከተት አዝ፦ አቤት እንዴት ታላቅ ነህ? እንዴት ታማኝ ነህ? እንዴት ፍፁም ነህ? የዘለዓለም አምላክ የማትለወጥ የፍቅር አምላክ ጸንተህ ትኖራለህ ሌት በመኝታ እንዳስብህ አንተን ቀን በሥራዬ እንዳውጠነጥን ነህና ለነፍሴ ዕርካታና ደስታ ክብርህን ላስበው ሁሌ ጠዋት ማታ አዝ፦ አቤት እንዴት ታላቅ ነህ? እንዴት ታማኝ ነህ? እንዴት ፍፁም ነህ? የዘለዓለም አምላክ የማትለወጥ የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ እጄን በአፌ ላይ አድርጌ ተደነቅሁ ሥራህንም ሳየው በደስታ ተሞላሁ በዕውነት ተረዳሁ የአንተን ታላቅነት እንዲሁም አስተዋልሁ የእኔን ውዳቂነት አዝ፦ አቤት እንዴት ታላቅ ነህ? እንዴት ታማኝ ነህ? እንዴት ፍፁም ነህ? የዘለዓለም አምላክ የማትለወጥ የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ ለአንተ ሚገባህ ክብርን ለመስጠት በመንፈስ ሳስብህ ያኔ ተረዳሁት አሁን ቃል ኪዳኔ የመጨረሻው ተዋርጄ እንድኖር ነው ለአንተ ምሻው አዝ፦ አቤት እንዴት ታላቅ ነህ? እንዴት ታማኝ ነህ? እንዴት ፍፁም ነህ? የዘለዓለም አምላክ የማትለወጥ የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ (2x)