ምክንያት አላቀርብም ለኃጢአቴ ራሴን አውቀዋለሁ ማንነቴን አንተ ግን ጻድቅ ነህ ለዘላለም ታውቀኛለህና የትም አልሄድም አሳዝኜኃለው እውነት ነው አላስከበርኩህም አውቃለሁ ነገርግን ጌታ ሆይ ማረኝ እላለሁ ምሕረትህ ብዙ ነው አንፃኝ ነፃለሁ ከፊትህ አትጣለኝ ከቶ ዝም አትበለኝ ቅዱሱን መንፈስህን ከኔ አትውሰድብኝ መለወጥ እሻለሁ ከኃጢአቴ አንፃኝ በደምህ እጠበኝ እኔም ነፃለሁ ኃጢያተኝነቴ እጅግ አሳዝኖህ ትተኸኝ እንዳትሄድ ለፈቃዴ ሰጥተህ እኔ ባሳዝንህ አትተወኝ እባክህ መሐሪ ነህና በእጅህ ላይ ጣለኝ አሳዝኜኃለው እውነት ነው አላስከበርኩህም አውቃለሁ ነገርግን ጌታ ሆይ ማረኝ እላለሁ ምሕረትህ ብዙ ነው አንፃኝ ነፃለሁ ኃጢያተኛን ትተህ ጨክነህ ብትሄድ ማን ይመልሰዋል ከሲኦል መንጋ እኔ ወደ ሲኦል ብሄድ ማን ያድነኛል በእጅህ ላይ መጣል እሱ ይሻለኛል