Song Lyrics

ጌታ ሆይ

Dawit Getachew
Tebikihalew
ሽክሜን እና ጭንቀቴን በፊትህ ይዤ እቀርባለሁ ላለፈው ይበቃኛል መለወጥ እኔ እሻለሁ አዝ:- ጌታ ሆይ የልመናዬን ቃል ስማ ፀሎቴንም መልስልኝ እጅህን ዘርግተህ ታደገኝ በእራሴ ብዙ ደክሜያለሁ ስለፋ የማላውቀውን በተስፋ ዕድሜዬን ሙሉ ስለፋ የአንተን የልብህን ሃሳብ እየፈጸምኩኝ መኖር እሻለሁ ከዚህች ዓለም ከንቱ ነገር ዐይኔንም አነሳዋለሁ ዋጋ አለውና የከበረ እርሱን ለመያዝ እዘረጋለሁ ከእንግዲህ በቀረኝ እድሜ ክብርህን ማየት እሻለሁ ባለማስተዋል የሰበሰብኩት ከንቱ ብቻ ነው ለካስ ያከማቸሁት ክፋቴን ሁሉ ዞር ብዬ ሳየው እራሴን ስወቅስ ደግሞ እገኛለሁ ደግም እንደገና ነግቶልኝ ስሮጥ አንድ ዐይነት ሕይወት የማይለወጥ የህ ከንቱ ኑሮ ብዙ ደከመኝ አሁን ግን በቃኝ ባክህ ለውጠኝ አዝ:- ጌታ ሆይ የልመናዬን ቃል ስማ ፀሎቴንም መልስልኝ እጅህን ዘርግተህ ታደገኝ በእራሴ ብዙ ደክሜያለሁ ስለፋ የማላውቀውን በተስፋ ዕድሜዬን ሙሉ ስለፋ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection