Song Lyrics

ናፍቃለሁ

Dawit Getachew
Tebikihalew
ኃያላን ሲነሱ እርስ በዕርሳቸው ምድር ስትናወጥ ግራ ሲገባቸው ቀኑ ሲደርስ ግን አንተ ስትመጣ ያን ጊዜ ያበቃል የዚች ዓለም ጣጣ አዝ:- ናፍቃለሁ ያንን ቀን ላይ ሁልጊዜ እሮጣለሁ የተሰቀለውን የሞተውን የተነሳውን ላየው የመላዕክት ድምፅ ዝማሬያቸው ከሩቁ ይሰማኛል የምጠብቀው ጌታ ኢየሱስ መምጫው ጊዜ ደርሷል ሁሉ በሁሉ ነው ምንም አይጐድለንም በሰማይ ቤት ስቃይ ጉስቁልና የለም እንዘምራለን ዘለዓለም በደስታ ለይሁዳ አንበሳ ሞትን ድል ለነሳ አዝ:- ናፍቃለሁ ያንን ቀን ላይ ሁልጊዜ እሮጣለሁ የተሰቀለውን የሞተውን የተነሳውን ላየው የመላዕክት ድምፅ ዝማሬያቸው ከሩቁ ይሰማኛል የምጠብቀው ጌታ ኢየሱስ መምጫው ጊዜ ደርሷል ጌታ ሲመጣ በመላእክት ታጅበን ከሙሽራው ጋር ልንኖር አብረን እንሄዳለህ የሚያሰጋን የለም ዕዳችን ሁሉ ተከፍሏል በነጽነት ልንኖር ከእርሱ ጋር ዳግመኛ በክብር ይመጣል (2x) ጌታ ሲመጣ በመላእክት ታጅበን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection