Song Lyrics

ለሥምህ

Dawit Getachew
Tebikihalew
ትዝ ይለኛል የማልረሳው ብዙ ታሪክ አለኝ ራሴን አውቃለሁ ማንነቴን ከየት እንዳነሳኝ ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስታውሰው ያለፈውን ሁሉ ስታግዘኝ ያዩ ዓይኖቼ በእንባ ይሞላሉ ክብር ለሥምህ ይሁን እዚህ አደረስከኝ ቀን ይመሻል ደግሞ ይነጋል ሁሉም ነገር ያልፋል ትዝታውን ግን ለመርሳት ከቶ እንዴት ይቻላል ባትደርስልኝ ባትዘረጋው የምህረት እጅህን ሳስበው እፈራለሁ መጨረሻዬን ክብር ለሥምህ ይሁን እዚህ አደረስከኝ በደስታ በሀዘኔ ከቶ ሳትለየኝ ተሸከምከኝ እዚህ አደረስከኝ ቀኖቹ ቢያልፉ መቼም አይረሳኝ ዛሬ ቆሜ ዘምረዋለሁ ለእኔ ያደረከው ብዙ ነው አንዳች የለም ከእኔ ነው የምለው አመሰግንሃለሁ ሁሉም አልፎ ዛሬ ቆሜያለሁ ከአንተ የተነሳ እዚህ አለሁ ስለነገ እንዴት እፈራለሁ ሕይወቴ በእጅህ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection