Song Lyrics

ድሮ ግና

Dawit Getachew
Tebikihalew
ድሮ ገና ከማህፀን ሳለሁ በእናቴ ሆድ በሥም ጠርተህ የለየኸኝ ክፉን ደጉን ሳላውቅ የአንተ ክብር መገለጫ እንድሆን በቤትህ ከነኃጢአቴ የመረጥከኝ ለአንተ እንድኖርልህ በሰጠኸኝ መንገድ ስሄድ ባሰብክልኝ ስፍራ እንዳልገኝ ሳሳዝንህ ቸል ብዬ ሳልሰራ ዛሬ በቀን ለምንሃለሁ ኃይልህ እንዲረዳኝ በመክሊቴ ብዙ አትርፌ አንተን ደስ እንዳሰኝ አዝ:- ኃይልህ ይርዳኝ ለምናለው እንድትረዳኝም አምናለሁ መልካም ነገር ያደረኩኝ መስሎኝ ሳሳዝንህ እንዳልገኝ ስመላለስ በዚህች ምድር ሳገለግል አንተን ለማልኖረውን አውርቼ የተጣልኩ እንዳልሆን እንዳታልፈኝ እፈራለሁ በምትመጣበት ቀን ሕይወቴማ አንተን ያክብድህ አፌ ብቻ ሳይሆን ክብርህን አሳየኝ የአንተን ማንነት ቅዱሱን መንፈስህን ሚመራኝ ወደ እውነት እኔ ደካማና ኃጢአተኛ ሰው ነኝ ሃይልህ ግን ከረዳኝ ከእግሬ እቆማለሁ አዝ:- ኃይልህ ይርዳኝ ለምናለው እንድትረዳኝም አምናለሁ መልካም ነገር ያደረኩኝ መስሎኝ ሳሳዝንህ እንዳልገኝ ቀድመህ ውጣ በሕይወቴ ልከተልህ ቸሩ አባቴ አንተ ቀድመኀኝ ካልወጣህ እኔ ብሮጥ ምን ላመጣ ለምንሃለሁ ጌታ ለምንሃለሁ ኢየሱስ ኃይልህ ይርዳኝ ጌታ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection