ከአድማስ ባሻገር ከዓይናችን የራቀ ከሩቁ ስናየው ሰማዩ ወደቀ ነገር ግን የአራቱም መጨረሻ አንተ ነህ ፍጥረት እጅህ ላይ ነው ምን ያህል ትልቅ ነህ አዝ:- በእውነት እኛም አናውቅህ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ ከአእምሮአችን በላይ ጥልቅ ነው ችሎታህ ሥራዎችን ሁሉ ስለ አንተ አወሩ ይሁን ስትላቸው ሆኑ ፍጥረታት በሙሉ ክብር ለሥምህ ይሁን ንፋስ በምድር ላይ እንዴት ይበተናል የበረዶው ክምር ማን አጥቦ አፅድቶታል ምድርን ስትሰራ ማን ነበረ አብሮህ እንዲህ አድርግ ብሎህ ማንስ አማከረህ አዝ:- በእውነት እኛም አናውቅህ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ ከአእምሮአችን በላይ ጥልቅ ነው ችሎታህ ሥራዎችን ሁሉ ስለ አንተ አወሩ ይሁን ስትላቸው ሆኑ ፍጥረታት በሙሉ ክብር ለሥምህ ይሁን ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑህ እልፍ እእላፍ መላእክቶች ወድቀው የሚሰግዱልህ በእውነት አንተ እግዚአብሔር ነህ (2x) አዝ:- በእውነት እኛም አናውቅህ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ ከአእምሮአችን በላይ ጥልቅ ነው ችሎታህ ሥራዎችን ሁሉ ስለ አንተ አወሩ ይሁን ስትላቸው ሆኑ ፍጥረታት በሙሉ ክብር ለሥምህ ይሁን (2x)