በማዕበል ውስጥ ሆኖ ከአንተ ጋራ መሄድ ነው (2x) በወጀብም መሃል ከአንተ ጋራ መሄድ ነው መሄድ ነው በባሕር ላይ ሆኖ ከአንተ ጋራ በሚያስፈራራው ተሽመድምዶ መቅረት ለምንድን ነው ግራ እንደገባው ከቶ ለምን ይሆን ከአንተ ጋራ የምንፈራው የዘወትር ልመና አሃሃሃ የምናደርሰው አዝ:- ጌታ ሆይ እባክህ ዓይኖቻችንን ክፈተው በእውነት ከእኛ ጋራ መሆንህን እንድናውቀው (2x) አንተ እያለህ ሁሉን ቻይ ከጐናችን እንፈራለን ወጀብን እያየን እምነታችንም በሁኔታዎች ጥለን ወየሁ ጠፋን እያልን እንጮሃለን ከእንግዲህ ከአንተ ጋር ቀና ብለን እንሄዳለን ወጀቡን እንፈራውም በስምህ እንረግጠዋለን ለአእዋፍ ሁሉ የምታጠግብ ነህ ለእኛ ለልጆችህ እንዴት ትነሳለህ ብታደርግ ሁልጊዜ አሃ መች እናውቅሃለን ስለሚቀጥለው ደግሞ ብዙ እናስባለን ጌታ አንተን ብናይ አሃ ይህ ባልሆነ በእኛ እምነት ጨምርልን ጌታ ሆይ ምነው አናውቅህምና አዝ:- ጌታ ሆይ እባክህ ዓይኖቻችንን ክፈተው በእውነት ከእኛ ጋራ መሆንህን እንድናውቀው (2x) አንተ እያለህ ሁሉን ቻይ ከጐናችን እንፈራለን ወጀብን እያየን እምነታችንም በሁኔታዎች ጥለን ወየሁ ጠፋን እያልን እንጮሃለን ከእንግዲህ ከአንተ ጋር ቀና ብለን እንሄዳለን ወጀቡን እንፈራውም በስምህ እንረግጠዋለን አንፈራም ወጀቡን አንፈራም አንፈራም