Song Lyrics

አንድ ቀን

Dawit Getachew
Tebikihalew
ድግስ አዘጋጅቷል ንጉሡ በይፋ ያላወቀ ሁሉ በከንቱ እንዳይለፋ ለሚገባው ሁሉ በእውነተኛው በር መንገዱ አንድ ነው የለም ከእርሱ በቀር ልብሳችንን አጥበን አጽድተን በደሙ ተግተን እንጠብቀው ቅርብ ነው ሰዓቱ አዝ:- አንድ ቀን አምላኬን እገናኘዋለሁ ሚያየኝን ጌታ እኔ አየዋለሁ በደስታ ሁሌ በፊቱ እዘምራለሁ ዘለዓለም ከእርሱ ጋር እኖራለሁ እንዴት ግሩም ቀን ነው ጌታን የማይበት ከዚህች ዓለም ስቃይ ከቶ የማርፍበት ኢየሱስ ይመጣል ታጅቦ በክብር አብረን እንሄዳለን ልንኖር ከእርሱ ጋር አዝ:- አንድ ቀን አምላኬን እገናኘዋለሁ ሚያየኝን ጌታ በዐይኔ አየዋለሁ ከደመና ከፍ ካለው በላይ እሄዳለው ዘለዓለም ከእርሱ ጋር እኖራለሁ እንዴት ብሩህ ቀን ነው ያን ቀን አብረን እንሄዳለን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection