Song Lyrics

በምህረቱ

Dawit Getachew
Tebikihalew
ኃጥያተኛ ነበርኩ ዓለም ጉድ ያለልኝ ለሰራሁት በደል ሞት የፈረዱብኝ ገበናዬን ገልጠው እየገፈተሩኝ ለፍርድ አቀረቡኝ በድንጋይ ሊወግሩኝ ዳኛው ግን ስለ እኔ በእውነት አዘነልኝ ውስጡን እያወቀ ለእኔ ፈረደልኝ ከከሳሾቼ እጅ በጥበብ አስጥሎኝ በእኔ ፋንታ እርሱ ሞቶ ከፈለልኝ አዝ:- በምህረቱ ዛሬ ቆሜያለሁ ስለ እኔ ሞቶ እኔ ድኛለሁ ነፍሴን ከሚሹ ከከሳሾቼ ማምለጥ ችያለሁ ምህረት አግኝቼ ስለ እኔ ሞቶ እኔ ድኛለሁ የምህረቱ ብዛት ከባሕር ይጠልቃል ስለኀጢያተኛው በእውነት ግድ ይለዋል እርሱ ነው ዳኛዬ የሆነኝ ጠበቃ ቀድሞ የታደገኝ ሕይወቴ ሲያበቃ ከሳሾቼ ሁሉ ድንጋያቸውን ጥለው ወደ ኋላ ሸሹ ህሊና ወቅሷቸው ስራዬን ሰርቶታል አሁን ነጻ ሰው ነኝ ላዳነኝ ኢየሱስ እዘምራለሁኝ አዝ:- በምህረቱ ዛሬ ቆሜያለሁ ስለ እኔ ሞቶ እኔ ድኛለሁ ነፍሴን ከሚሹ ከከሳሾቼ ማምለጥ ችያለሁ ምህረት አግኝቼ ዋጋዬ ይሄ ነው በእርሱ ደም ታጥቤያለሁ እኔ ድኛለሁ ስለ እኔ ሞቶ አድኖኛል በእርሱ ቁስል ተፌውሻለሁ ነፍሴን ከሚሹ ከአዳኝ ወጥመድ አስመለጠኝ አኔን አዳነኝ ዛሬ በደስታ ዘምራለሁ በእርሱ ቁስል እኔ ድኛለሁ ፍቅሩን እያሰብኩ በፊቱ ዘምራለሁ ከሞት አፍ ከጫፍ ላይ አውጥቶኛልና ታሪኬን አወራለሁ ምህረቱን እያሰብኩ በፊቱ ዘምራለሁ ለነፍሴ መዳን ሆኖላታልና ሥሙን እባርካለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection