Song Lyrics

ዘለዓለም

Dawit Getachew
Tebikihalew
ሥራህን ለመግለፅ አንደበት ቢያንሰኝም ከምሥጋና በቀር የምለው የለኝም ሳወራው እኖራለሁ እስከ ለዘለዓለም ያደረከው ሁሉ ከልቤ አይጠፋም ጊዜው ቢርቅ ብዙ ቢያልፍም ከልቤ ውስጥ ከቶ አይጠፋም ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም ትዝ ይለኛል እስከ ዘለዓለም አዝ:- ዘለዓለም አይጠፋም ኢየሱስ ፍቅርህ ያደረከው ሁሉ ዉለታህ ከቶ አልረሳውም ታትሟል በልቤ የዘለዓለም ፍቅሬ ነህ ወዳጄ መገረፍ መድማትህ ለእኔ መሞትህ ከጥፋት እንዳመልጥ ከክብርህ መውረድህ ከተወጋው ጐንህ የፈሰሰው ደምህ ዘወትር ትዝ ይለእኛል ኢየሱስ መከራህ የመስቀሉ ዉለታህ ለእኔ ትልቅ ትዝታ ነው መድህኔ ሕይወትን ሰጥተህ አድነኀኛል ፍቅርህ ከልቤ ወስጥ እንዴት ይጠፋል አዝ:- ዘለዓለም አይጠፋም ኢየሱስ ፍቅርህ ያደረከው ሁሉ ዉለታህ ከቶ አልረሳውም ታትሟል በልቤ የዘለዓለም ፍቅሬ ነህ ወዳጄ (2x) ዓይኔ ሌላ ከቶ አያይም ምርጫዬ ነህ ለዘለዓለም ፍቅርህ ልቤን ውስጥ ሰርጾ ገብቷል ማንም ሳይቀይረው ይኖራል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection