Song Lyrics

እጠብቅሃለሁ

Dawit Getachew
Tebikihalew
ሰምቼ ነበረ ስታንኳኳ በሬን ግን አላስተዋልኩም አንተ መሆንህን ብዙ አድክሜሃለሁ አውቃልሁ እራሴ ግን እራርተህልኝ ቤቴ ትመጣ ይሆን አዝ:- እጠብቅሃለሁ ጌታ ባስቀመጥከኝ ቦታ በመጠበቂያዬ ላይ ዳግም እስክትመጣ ድምፅህን አሰማኝ ልቤ እንዲፅናና ግን አንተ ዝም ካልከኝ እፈራለሁና ዝም ስትል ጊዜ ስታጠፋ ድምጽህን ያሰብኩት በሙሉ እንዳልነበር ሲሆን ቀኑ ሲጨላልም ፈርቼ ይህን ሁኔታ መልዕክት ልኬ ነበር ትመጣ ይሆን የሚል አዝ:- እጠብቅሃለሁ ጌታ ባስቀመጥከኝ ቦታ በመጠበቂያዬ ላይ ዳግም እስክትመታ ድምፅህን አሰማኝ ልቤ እንዲፅናና ግን አንተ ዝም ካልከኝ እጠፋለሁና እንግዳዬ ኢየሱስ እረፍ ቤቴ ገብተህ ብዙ የምነግርህ አለኝ ማጫውትህ ልቤ አንተ ቤት ነው ሀሳብህን ፈፅም እጠብቅሃለሁ ከቶ አልሰለችም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection