ሁኔታዎችን አይቼ ተመስገን አልልህም ያሰብኩት ባይሳካ አፌን አላበላሽም እግዚአብሔር አንተ በእውነት ጻድቅ ነህ የሚሳንህ አንዳች የለም ይሆናል አይሆን ብዬ በዚህ አልገመግምህም ለባህር ገደብን ሰጠህ ከዚህ አትለፍ ብለህ ፀሀይም በማለዳ በቃልህ ያጸና አንተ ስትናገር የማይሆን የቱ ነው ሁኔታን አይቼ ክፉ አይወጣኝም ሁሉም ነገር በእጅህ ነው አንተ ለእኔ ያለህ አላማ መልካም ነው ለዘለዓለም በሞት ጥላ ውስጥ ብራመድ ክፉውን እኔ አልፈራም ብታድነኝ ባታድነኝም ብትሰጠኝ ብትነሳኝም አምልኮ ስራዬ እንጂ የሕይወቴ ጊዜያዊው ስሜት አይደለም ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በስራህ አትሳሳትም አማካሪ አትፈልግ የትኛው ነገር አቅቶህ ስለዚህ ራሴን እንቃለው በምትሰራው ስራ ምህረትህ ለእኔ ይብዛልኝ ለሃጥያቴ ከማውቅህ በላይ ነህና