ነጋ ሌሊቱ አለፈና ዳግም ቆምኩኝ እኔም ለምስጋና እነዚያ ቀናቶች አለፉ እግዚአብሄር ከልሎኝ ከክፉ እነዚያ ሌሊቶች አለፉ ምህረቱ ሸሽጎኝ ከክፋ በጨነቀኝ ግዜ ወደ አምላኬ ጮህኹኝ ጩኸቴንም ሰምቶ ፈጥኖ ደረሰልኝ በእኔ እና በሞት አንድ እርምጃ ሲቀር የምህረት እጁ ነው የያዘኝ በፍቅር ያወጣኝ በፍቅር እንዴት እሆን ነበር ባይደርስልኝ ከገኔ ጠላት በዋጠኝ በጠፋሁኝ ነበር ያኔ እንዴት እሆን ነበር ዞር ብዬ እያሰብኩኝ ለአዳነኝ ፀጋ መስጋናን እሰዋለሁኝ የምህረቱ ብዛት በህይወት አቆመኝ እንጂ በእራሴማ ትናንትን ባልኖርኩኝ ዛሬን ባላየሁኝ ለነገም ተስፋዬ እግዚአብሔር ነውና ስሙን እባርካለሁ በብዙ ምስጋና የማያልፍ ከሚመስል የህወቴ ሌሊት ፈጥኖ የታደገኝ ሰው ከማይደርስበት እግዚአብሔር ነው የህይወቴ ብርሀን የእንደገና አምላክ የሰጠኝ ሌላ እድልን በክንፎቹ መሀል አዝሎ አሻገረኝ ብቻውን እየመራ እዚህ አደረሰኝ ተጠነቀቀልኝ እንደ አይኑ ብሌን ጸጋና ምህረቱን አብዝቶ ያለመጠን አምላክ አለኝ የሚራራልኝ ገና ሳልነግረው የሚረዳኝ አይኑ እንዳየ የማይፈርድ ለዘላለምም የሚወድ ባለቀስኩበት ቀናት ፈንታ ልቤን ሞላው በእልልታ የዘወትር ዋና ስራዬ ምስጋናው ሆኗል የጌታዬ